የታንዛኒያ ምክትል ፕሬዝዳንት አዲስ አበባ ገቡ

ጥር 27/2014 (ዋልታ) የታንዛኒያ ምክትል ፕሬዝዳንት ፊሊፕ ሞፓንጎ (ዶ/ር) ፕሬዝዳንት በ35ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባኤ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገቡ።

ምክትል ፕሬዝዳንቱ ቦሌ ዓለም ዐቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ፣ የሀገር መከላከያ ሚኒስትር አብርሃም በላይ (ዶ/ር)፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ እና ሌሎች ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።

በሜሮን መስፍን

 

ለፈጣን መረጃዎች፦

ፌስቡክ https://www.facebook.com/waltainfo

ቴሌግራም https://t.me/WALTATVEth

ዩቲዩብ https://www.youtube.com/c/WaltaTV/featured

ቲዊተር https://twitter.com/walta_info

አብራችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን!