የሶማሊያ ፕሬዝዳንት መሀመድ አብዱላሂ ፋርማጆ አዲስ አበባ ገቡ

                                                  ፕሬዝዳንት መሀመድ አብዱላሂ ፋርማጆ

ጥር 27/2014 (ዋልታ) የሶማሊያ ፕሬዝዳንት መሀመድ አብዱላሂ ፋርማጆ በ35ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባኤ ለመሳተፍ ዛሬ አዲስ አበባ ገብተዋል።

ፕሬዝዳንቱ በቦሌ ዓለም ዐቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርሱ የግብርና ሚኒስትሩ ኡመር ሁሴን አቀባበል አድርገውላቸዋል።

በተጨማሪም የመከላከያ ማርች ቡድን፣ ከየክልሉ የመጡ የባህል ቡድን አባላት እንዲሁም ሰርከስ አቅራቢ ወጣቶች በአቀባበል ስነሥርዓት ላይ የተለያዩ ጥዑመ ዜማ በማሰማት መቀበላቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

35ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባኤ “የአፍሪካ አኅጉርን የሥርዓተ ምግብ አቅም መገንባት፤ የሰው ሃብት ልማት፣ የኢኮኖሚና ማኅበራዊ ልማትን ያፋጥናል” በሚል መሪ ሃሳብ ቅዳሜና እሁድ ይካሄዳል።

ለፈጣን መረጃዎች፦

ፌስቡክ https://www.facebook.com/waltainfo

ቴሌግራም https://t.me/WALTATVEth

ዩቲዩብ https://www.youtube.com/c/WaltaTV/featured

ቲዊተር https://twitter.com/walta_info

አብራችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን!