ም/ጠ/ሚኒስትር ደመቀ መኮንን የዓለም ዐቀፍ አቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ጋር ተወያዩ

ጥር 27/2014 (ዋልታ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን የዓለም ዐቀፍ አቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ራፋኤል ማሪያኖ ጋር ተወያዩ፡፡

ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ የአፍሪካ ኅብረት ስብሰባን በስኬት በማስተናገድ ላይ እንደምትገኝ ጠቅሰው ይህም በአገሪቱ ያለውን ሰላም አመላካች መሆኑን አንስተዋል።

የአቶሚክ ኃይልን ለልማት ለመጠቀምና ትብብሩን ለማጠናከር ኢትየጵያ ፍላጎት እንዳላት መግለጻቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽሕፈት ቤት የተገኘው መረጃ አመላክቷል፡፡

የዓለም ዐቀፍ አቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ራፋኤል ማሪያኖ በበኩላቸው በዛሬው ቀን ተከብሮ የሚውለውን የዓለም ዐቀፍ የካንሰር ቀን አውስተዋል።

ካንሰር በዓለም ዐቀፍ ደረጃ የሚያደርሰውን ከፍተኛ የጤና ጉዳት በመጥቀስ ኤጀንሲያቸው በኢትዮጵያ የካንሰር ህክምና ማዕከል የማቋቋም እቅድ እንዳለውም ገልጸዋል።