የቻድ ጠቅላይ ሚኒስትር አልበርት ፓሂሚ ፓዳኬ አዲስ አበባ ገቡ

ጥር 27/2014 (ዋልታ) የቻድ ጠቅላይ ሚኒስትር ፓሂሚ ፓዳኬ በ35ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባኤ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገብተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩና የልዑካን ቡድናቸው ቦሌ ዓለም ዐቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የመስኖና ቆላማ አካባቢዎች ሚኒስትር አይሻ መሐመድ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደርብርቱካን አያኖ እና ሌሎች ከፍተኛ የመንግሥት አመራሮች አቀባበል ማድረጋቸውን ኢዜአ ዘግቧል።