በመንግሥታቱ ምክትል ዋና ጸሐፊ የተመራ ልዑክ ኮምቦልቻ ገባ

ጥር 29/2014 (ዋልታ) በተባበሩት መንግሥታት ምክትል ዋና ጸሐፊ አሚና መሃመድ የተመራ የመንግሥቱ ልዑክ ኮምቦልቻ ገባ፡፡
የአማራ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር ጌታቸው ጀምበር (ዶ/ር) እና የክልሉ ምክር ቤት አፈጉባኤ ፋንቱ ተስፋዬ እና ሌሎች ከፍተኛ ባለሥልጣናት ለልዑኩ አቀባበል አድርገዋል።
እንደ ኤፍቢሲ ዘገባ ልዑኩ በትሕነግ የሽብር ቡድን የወደሙ አካባቢዎችን ከጎበኘ በኋላ በጉዳዩ ላይ ገለጻ ይደረግለታል ተብሎ ይጠበቃል።