ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ያስገነባውን የመምህራን መኖርያ ቤት ለመምህራን አስረከበ

ጥር 29/2014 (ዋልታ) ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ከ500 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ ያስገነባውን የመምህራን መኖሪያ ቤቶች ለመምህራን አስረከበ።
የመኖሪያ ቤቶቹ በዩኒቨርሲቲው ለሚያገለግሉ ከ250 በላይ መምህራን መተላለፋቸውም ተገልጿል።
የመኖሪያ መንደሩ በዩኒቨርሲቲው አቅራቢያ የተነገባ መሆኑ የመምህራኑን ህይወት ከማቃለሉም በተጨማሪ ጊዜና ገንዘብ በመቆጠብ የመማር ማስተማር ሥራውን የሚያቀላጥፍ እንደሆነ ተነግሮለታል።
የመኖሪያ መንደሩ አስፈላጊ የሚባሉ የመሰረተ ልማቶች የተሟሉለት መሆኑን የተናገሩት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ፋሪስ ደሊል (ዶ/ር) በቀጣይም ዘመናዊ የኑሮ ዘይቤን ያማከለ እንዲሆን አስፈላጊው ግንባታ እየተደረገለት እንደሚሄድ አስረድተዋል፡፡
መምህራኑ ልጆቻቸውን የሚያስተምሩበት የአንደኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለመገንባት የሚያስችል የንድፍ ሥራ መጠናቀቁንም ገልፀዋል።
በሚልኪያስ አዱኛ (ከወልቂጤ)