ኅብረቱ በአፍሪካ አገራት ላይ የሚጣሉ ማዕቀቦቸን አወገዘ

ጥር 30/2014 (ዋልታ) የአፍሪካ ኅብረት በተለያዩ አገራት በኩል አባል አገራቱ ላይ ጫና ለማሳደር በማለም እየተጣሉ የሚገኙ ማዕቀቦችን አወገዘ።

ኅብረቱ 35ኛውን የመሪዎች ጉባኤ ተከትሎ ከማዕቀቦች ጋር በተያያዘ ባወጣው ረቂቅ የውሳኔ ሐሳብ አባል አገራቱ ላይ የሚጣሉ የተናጠል ማዕቀቦችን በመቃወም ሊታረሙ እንድሚገባ ገልጿል።

በተናጠል የሚጣሉ ማዕቀቦች ከዓለም ዐቀፍ ሕጎቸ ጋር የሚቃረኑ የአገራትን ግንኙነትም የሚፃረሩ ናቸው ብሏል።

የአገራት የተናጠል አስገዳጅ ማዕቀቦች የአገራትን የድኅረ ግጭት መልሶ ግንባታና የሰላም ሂደት በጉልሁ የሚጎዱ ናቸው ሲለም ኮንኗል።

በአገራት ላይ የፖለቲካ፣ ምጣኔሃብትና ሌሎችም ጫናዎችን ለማሳደር ታልሞ እየተጣለ የሚገኘው የአንዳንድ አገራት የተናጠል ማዕቀብ የአባሎቼን ራስን የመበየንና ማስተዳደር መብት የሚፃረር ነው ሲልም ባወጣው መግለጫ በፀኑ አውግዟል።
ለፈጣን መረጃዎች፦