የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አዲስ ያስገነባውን ህንፃ እሁድ ያስመርቃል

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

የካቲት 1/2014 (ዋልታ) የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን 80ኛ ዓመት የምስረታ በዓል እና የአዲሱን ዋና መሥሪያ ቤት ህንፃ ምርቃትን አስመልክቶ የባንኩፕሬዝዳንት አቤ ሳኖ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

በመግለጫቸውም ባንኩ አዲስ ያስገነባውን ዋና መስሪያ ቤት በመጪው እሁድ እንደሚያስመርቅ አስታውቀዋል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ተመስርቶ አገልግሎት መስጠት ከጀመረ 80 ዓመታትን ያስቆጠረ ሲሆን ባንኩ ያስገነባው የዋና ምሥሪያ ቤት ህንፃ በቁመቱ ከምስራቅ አፍሪካ ቀዳሚ እንዲሁም በአፍሪካ 7ኛውን ደረጃ የያዘ ግዙፍ ህንፃ እንደሆነ ተነግሮለታል።