ለፈረንሳይ ሴናተሮችና የውጭ ግንኙነት ኮሚቴ አባላት ስለኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ገለጻ ተደረገ

የካቲት 1/2014 (ዋልታ) በፈረንሣይ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሄኖክ ተፈራ ለፈረንሣይ ሴናተሮች እና የውጭ ግንኙነት ኮሚቴ አባላት ስለኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ገለጻ አድርገዋል።

በገለፃቸው የኢትዮጵያ መንግሥት የብሔራዊ ምክክር ኮሚሽን በማቋቋም እና ከፍተኛ የፖለቲካ ሰዎችን ከእስር እንዲፈቱ በማድረግ ሰላምን ለማስፈን በቁርጠኝነት እየሠራ መሆኑን አብራርተዋል።

አሸባሪው ሕወሓት በአዲስ መልክ በአፋር እና በአማራ ክልሎች እያደረሰ ባለው ጥቃት የሰላም ጥረቶችን እና ሰብኣዊ እርዳታዎችን እያደናቀፈ መሆኑንም ገልፀዋል።

ፈረንሣይ የኢትዮጵያን የመልሶ ማቋቋም ጥረት እና የታቀደውን ብሔራዊ ምክክር ለመደገፍ እያሳየችው ላለው ዝግጁነትም አምባሳደር ሄኖክ ሀገራቸውን በመወከል ምስጋና ማቅረባቸውን በፓሪስ ከኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።