በጦርነቱ በኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት 1ነጥብ 64 ቢሊዮን ብር በላይ ሃብት ወድሟል

የካቲት 02/2014 (ዋልታ) በጦርነቱ ምክንያት በኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት ላይ 1 ነጥብ 64 ቢሊዮን ብር በላይ ሃብት መውደሙን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታወቀ።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በሰጠው መግለጫ በጦርነት ቀጣና ውስጥ በነበሩት አፋር እና አማራ ክልሎች የሚገኙ 53 በመቶ ከፍተኛ የኤሌክትሪክ መስመሮች ጉዳት ደርሶባቸዋል ብሏል።

አጠቃላይ ጥገናውን ለማከናወን 23 ሚሊዮን ዶላር ያስፈልጋልም ተብሏል፡፡

በጦርነቱ ምክንያት ኤሌክትሪክ ተቋርጦ በነበረባቸው አብዛኞቹ አካባቢ የኤለክትሪክ ኃይል እንዲያገኙ ለማስቻል በ29 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር የጥገና ሥራ ስለመሰራቱ ኢብኮ ዝግቧል፡፡