ከሊባኖስ 61 ኢትዮጵያዊያን ወደ አገራቸው ተመለሱ

 

የካቲት 3/2014 (ዋልታ) በሊባኖስ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ቆንስላ ጄኔራል ጽህፈት ቤት ከሊባኖስ የኢሚግሬሽን ጋር በመነጋገር በተለያየ ምክንያት ያለ ህጋዊ ሰነድ በሊባኖስ ይኖሩ የነበሩ 61 ዜጎቻችንን ወደ አገራቸው እንዲመለሱ ተደርጓል።

የተመለሱት ዜጎች በ2014 ዓ.ም በጀት ዓመት በመጀመሪያ ዙር ተመዝግበው የነበሩ መሆናቸውንም ከውጭ ጉዳይ ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት የተገኘው መረጃ ያሳያል፡፡