ለ27 የብሔራዊ ቡድኑ ተጫዋቾች ጥሪ ተደረገ

የካቲት 6/2014 (ዋልታ) አሰልጣኝ ፍሬው ኃይለገብርኤል ለሴቶች ከ20 ዓመት በታች የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ውድድር ዝግጅት ለ27 ተጫዋቾች ጥሪ አደረጉ።

በኮስታሪካ አስተናጋጅነት በሚካሄደው የ2022 የሴቶች ከ20 ዓመት በታች ዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ከጋና አቻው ጋር ለሚጫወተው የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ዝግጅት ነው አሰልጣኙ ጥሪውን ያቀረቡት፡፡

ብሔራዊ ቡድኑ እስካሁን ያደረጋቸውን አራት የደርሶ መልስ የማጣሪያ ጨዋታዎች በማሸነፍ በቀጣይ ከጋና አቻው ጋር ለሚያደርገው የ5ኛው እና የመጨረሻው የማጣርያ ዙር ጨዋታ ከሰሞኑ ዝግጅት ይጀምራል፡፡

በዚህም የተጠሩ ተጫዋቾች ሰኞ የካቲት 7 ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጽሕፈት ቤት በመገኘት ሪፖርት እንዲያደርጉ ጥሪ እንደደረሳቸው ነው ፌደሬሽኑ ያሳወቀው፡፡