የምስራቅ አፍሪካ አገራት ጠቅላይ ኢታማዦር ሹሞች በሶማሊያ ግዳጅ አፈጻጸም ዙሪያ ተወያዩ

የካቲት 7/2014 (ዋልታ) ወደ ኢትዮጵያ የመጡት ″በአሚሶም‶ ግዳጅ ተሳታፊ የሆኑ የምስራቅ አፍሪካ አገራት ጠቅላይ ኢታማዦር ሹሞች በጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ሰብሳቢነት ተወያይተዋል።

ምክክሩ ከሶማሊያ ግዳጅ ጋር በተያያዘ የጋራ አረዳድ ለመያዝ ያለመ ነው ተብሏል።

በውይይታቸውም በሶማሊያ ስላለው ኃይል እንቅስቃሴና ለቀጣይ መደረግ ስላለበት ጉዳይ በጥልቀት መምከራቸው ተመላክቷል፡፡

አሁን ላይም በአፍሪካ ኅብረት የባለድርሻ አካላት ውይይት እየተካሄደ መሆኑም ተጠቁሟል፡፡

በውይይቱ የኢትዮጵያን ጨምሮ የኬንያ፣ ኡጋንዳ፣ ቡሩንዲ እና ሶማሊያ ጠቅላይ ኢታማዦር ሹሞች አና የጅቡቲ ምክትል ጠቅላይ ኢታማዦር የአሚሶም ፎርስ ኮማንደር መሳተፋቸውን የመከላከያ ሰራዊት መረጃ ያመለክታል።