የአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት ለድርቅ ተጎጂዎች ተጨማሪ 2 ቢለዮን ብር ድጋፍ አደረገ

የአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት

የካቲት 9/2014 (ዋልታ) የአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት (ዩኤስአይድ) በኢትዮጵያ ለተከሰተው ድርቅ ድጋፍ የሚውል ተጨማሪ 2 ቢሊየን ብር ወይም 39 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር ድጋፍ ማድረጉን አስታወቀ።

ድጋፉ ድርቅ በተከሰተባቸው የአማራ፣ ኦሮሚያ፣ ደቡብ እና ሶማሌ ክልሎች ጉዳት ለደረሰባቸው የማኅበረሰብ ክፍሎች እርዳታ የሚውል እንደሆነ ከተቋሙ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡