የሶማሌ ክልል ግማሽ ቢሊየን ብር ተጨማሪ በጀት እንዲፀድቅ ውሳኔ አሳለፈ

የካቲት 10/2014 (ዋልታ) የሶማሌ ክልል ካቢኔ ባካሄደው ስብሰባ 500 ሚሊየን ብር ተጨማሪ በጀት እንዲፀደቅ ውሳኔ አሳለፈ።

ተጨማሪ በጀቱ በሚቀጥሉት ወራት በክልሉ ለተከሰተው የድርቅ አደጋ ምላሽ የሚውል መሆኑ ተገልጿል።

በተለይም ለተለያዩ ምግቦች መግዣ፣ ለውሃ፣ ለጤናና ለእንስሳት መኖ አቅርቦት የሚመደብ ነው ተብሏል።

በተጨማሪም ካቢኔው በተለያዩ ደንቦችና ረቂቅ አዋጆች ላይ ውሳኔ በማሳለፍ ለክልሉ ምክር ቤት መርቷል፡፡

ካቢኔው ያፀደቀው ተጨማሪ በጀት፣ ደንቦችና አዋጆች ቅዳሜ የክልሉ ምክር ቤት በሚያደርገው ጉባኤ ከፀደቀ በኋላ ተግባራዊ እንደሚሆን የሶማሌ ክልል ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አብዱልቃድር ረሺድ ገልፀዋል።

መረጃው የሶማሌ ክልል ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ነው፡፡