አገራዊ ምክክሩ የሕዝቦች መወያያ መድረክ ሊሆን እንደሚገባ ተጠቆመ

የካቲት 10/2014 (ዋልታ) አገራዊ ምክክሩ የፖለቲካ ልሂቃን መደራደሪያ ብቻ ሳይሆን የሕዝቦች መወያያ መድረክ እንዲሆን በጥንቃቄ መሥራት እንደሚገባ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል ደሳለኝ ጫኔ (ዶ/ር) ተናገሩ።

እንደ ኢትዮጵያ ጠርዝ ላይ የቆሙ የፖለቲካ ኃይሎችና መጠራጠር የበዛበት ማኅበራዊ ግንኙነት ባለበት አገር ውስጥ አገራዊ ምክክር መደረጉ ፋይዳው የላቀ ነው ብለዋል።

ምክክሩ የጋራ እሴቶችን፣ አገራዊ ምልክቶችን ለመቅረፅና የጋራ ታሪክና ፍላጎቶችን ለማንፀባረቅ እንደሚያስችልም መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ምክክሩ ከየትኛውም አካል ተፅዕኖ ነጻ ሊሆን እንደሚገባና በየትኛውም ሀገራዊ ጉዳይ ላይ መነጋገርና መደማመጥ የሚቻልበት መድረክ ሊሆን እንዲገባም አሳስበዋል፡፡