የሲዳማ ክልል በኦሮሚያ ክልል በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች የ20 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ

የካቲት 10/2014 (ዋልታ) የሲዳማ ክልላዊ መንግሥት በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች የ20 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አድርጓል፡፡

ድጋፉን የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ ለኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ ማስረከባቸውን የኦቢኤን ዘገባ ያመለክታል፡፡