ሳማሪታንስ ፐርስ ለኢትዮጵያ የህክምና ቁሳቁሶችን ድጋፍ አደረገ

የካቲት 10/2014 (ዋልታ) ሳማሪታንስ ፐርስ የተሰኘው ዓለም ዐቀፍ ግብረሰናይ ድርጅት የህክምና ቁሳቁሶችን ለኢትዮጵያ ድጋፍ አደረገ።

የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ቦሌ ዓለም ዐቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በመገኘት ድጋፉን ተረክበዋል።

ድጋፉ በጦርነቱ ምክንያት የተጎዱ የጤና ተቋማትን መልሶ ለማቋቋም የሚውል መሆኑን ኢዜአ ዘግቧል።