ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከጀርመኑ ቻንስለር ጋር ተወያዩ

የካቲት 10/2014 (ዋልታ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከጀርመኑ ቻንስለር ኦላፍ ሹልዝ ጋር ተወያዩ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቲውተር ገጻቸው “ከኦላፍ ሹልዝ ጋር በተለያዩ የሁለትዮሽና የጋራ ጉዳዮች ላይ ስላደረግነው ጠቃሚ ምክክር አድናቆቴ ይድረስ” ሲሉ ጽፈዋል።

ኢትዮጵያ እስካሁን ጀርመን ያደረገችላትን የልማት ድጋፍ የምታደንቅ ሲሆን፣ ትብብራችንም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ጽኑ እምነት አላት ነው ያሉት።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቤልጄም የአፍሪካ ኅብረት – አውሮፓ ኅብረት ጉባኤ እየተሳተፉና የጎንዮሽ ውይይቶችን እናደረጉ ነው።