የካቲት 20/2014 (ዋልታ) ፖራዳይዝ ቫሊ ኮሌጅ አዳማ ቅርንጫፍ በ2012 ዓ.ም በትምህርት ጥራት መረጋገጫ ኤጄንሲ ህጋዊ ባልሆነ አሰራር ተዘግቶ እንደነበረና በፍርድ ቤት ብይን ዳግም ተከፍቶ በዛሬው ዕለት ወደ ሥራ መመለሱ ተገለጸ።
የኮሌጁ አዳማ ቅርንጫፍ ከየካቲት 4/2014 ዓ.ም ጀምሮ ወደ መደበኛ የመማር ማስተማር ሥራው እንዲመለስ ተወስኖለት በዛሬው ቀን በተለያዩ መረሃ ግብሮች የኮሌጁ ዳግም መከፈት ተበስሯል።
በሥነሥርዓቱ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የፓራዳይዝ ቫሊ ኮሌጅ ባለቤት አየለ ኮሮሶ ፍትህ ተረጋግጦ ኮሌጁ መከፈቱ እንዳስደሰታቸው ተናግረዋል።
በኮሌጁ የመማርና የሥራ ዕድል ያገኙ ግለሰቦች በበኩላቸው ኮሌጁ ደግም በመከፈቱ መደሰታቸውን ገልጸው የኮሌጁ ዳግም መከፈት ጉዳይ በፍትህ የተረጋገጠበት በመሆኑ ያኮራናል ብለዋል።
የፓራዳይዝ ቫሊ ኮሌጅ አዳማ ቅርንጫፍ ዲን ደስታ ቱፋ በበኩላቸው ከከዚህ በፊቱ በበለጠ በመሥራት ኮሌጁን ወደ ዩኒቨርሲቲ ለማሳደግ እንሰራለን ብለዋል።
ፓራዳይዝ ቫሊ ፍትህ ያገኘበትን ዕለት የካቲት 04 ቀን በየዓመቱ በበጎ አድራጎት ሥራ እንደሚያከብርም ተገልጿል።
በቡላ ነዲ