ጠ/ሚ/ር ዐቢይ እና ፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ መርቆሬዎስን በሆስፒታል ተገኝተው ጎበኙ

ጠ/ሚ/ር ዐቢይ

የካቲት 20/2014 (ዋልታ) ፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ እና ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ መርቆሬዎስን በዛሬው እለት በሆስፒታል ተገኝተው ጎብኝተዋል።

4ኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋኅዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ባጋጠማቸው ሕመም ምክንያት በሆስፒታል የሕክምና ክትትል እየተደረገላቸው እንደሚገኝ ተገልጿል።

ፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ በቀደመው ጊዜ የቅዱስነታቸው የመንፈስ ቅዱስ ልጅ መሆናቸውን ገልጸው በቶሎ ድነው ከሆስፒታል እንዲወጡ ምኞታቸውን መግለፃቸውን ኢኦቴቤ ጠቅሶ ኢቢሲ ዘግቧል።