የባህልና ስፖርት ሚኒስትር የዓድዋ ድል በዓለም አስደናቂ የታሪክ ክስተት ነው አሉ

የካቲት 21/2014 (ዋልታ) የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ቀጀላ መርዳሳ የዓድዋ ድል በዓለም አስደናቂ የታሪክ ክስተት ነው ሲሉ ገለጹ፡፡

የዓድዋ ድልን የሚዘክር የመዛግብት፣ የፎቶግራፍ እና የጽሑፍ ቅርስ አውደርእይ መክፈቻ ለይ የተገኙት ሚኒስትሩ የዓድዋ ድል ለመላው የጥቁር ሕዝቦች የነጻነት ጮራ የፈነጠቀ ነው ብለዋል።

በአውደርእይው የተሳተፉ የከተማዋ ነዋሪዎች በሰጡት አስተያየታቸው እንደነዚህ አይነት ትእይንቶች ዜጎች ስለታሪካቸው እንዲያውቁና እንዲመራመሩ የሚረዳ መሆኑን አንስተዋል፡፡

126ኛው የዓድዋ ድል መታሰቢያ በዓል “ዓድዋ ለኢትዮጵያ ኅብረት ለአፍሪካ የነጻነት ጮራ ነው” በሚል መሪ ሀሳብ በተለያዩ መርሃግብሮች እየተከበረ ይገኛል።

በአብርሆት ቤተ-መጽሐፍት ለሦስት ተከታታይ ቀናት የሚቆይ የዓድዋን ድል የሚዘክር አውደ-ርዕይ ዛሬ የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች በተገኙበት ለሕዝብ ክፍት ሆኗል፡፡

በመስከረም ቸርነት

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW