126ኛው የዓድዋ የድል በዓል በመላ ኢትዮጵያ እየተከበረ ነው

126ኛው የዓድዋ የድል በዓል

የካቲት 23/2014 (ዋልታ) 126ኛው የዓድዋ የድል በዓል የኢትዮጵያዊያ ኅብረት፤ የአፍሪካ የነፃነት ጮራ በሚል መሪ ሃሳብ በመላ ኢትዮጵያ እየተከበረ ይገኛል።

በዓሉ በተለይም በአዲስ አበባ በዳግማዊ ምኒልክ አደባባይ በድምቀት እየተከበረ ሲሆን በክብረ በዓሉ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ጃንጥራር አባይ፣ የከተማ አስተዳደሩ ባህልና ኪነጥበባት ቢሮ ኃላፊ ሂሩት ካሳው (ዶ/ር)፣ የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማኅበር ፕሬዝዳንት ልጅ ዳንኤል ጆቴን ጨምሮ ሌሎች ግለሰቦች ተገኝተዋል፡፡

በወቅቱም በሚኒሊክ ሐውልት የአበባ ጉንጉን አስቀምጠዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባህልና ኪነጥበባት ቢሮ ኃላፊ ሂሩት ካሳው (ዶ/ር) በመርሃ ግብሩ ላይ የእንኳን አደረሳቹህ መልዕክት አስተላልፈዋል።

በመልዕክታቸውም ይህ ትውልድ በኅዳሴ ግድብ ላይ ዳግማዊ የዓድዋ ድልን እያስመዘገበ ነው ብለዋል።