ፖሊስ 126ኛው የአድዋ ድል በዓል በሰላም መጠናቀቁን አስታወቀ

የካቲት 23/2014 (ዋልታ) በአዲስ አበባ ከተማ ሲከበር የነበረው 126ኛው የአድዋ ድል በዓል በሰላም መጠናቀቁን ፖሊስ አስታወቀ፡፡

የከተማዋ ነዋሪዎች ለፀጥታ አካላት ያሳዩት ተባባሪነት እና ያደረጉት ድጋፍ ለበዓሉ በሰላም መጠናቀቅ አስተዋፅኦው ከፍተኛ መሆኑን ከአዲስ አበባ ፖሊስ መረጃ አመላክቷል፡፡

ኃላፊነታቸውን በአግባቡ ለተወጡት የፀጥታ አካላት እና በተለያየ መልኩ የፀጥታውን ሥራ ለደገፉ በጎ ፈቃደኞች ፖሊስ ምስጋና አቅርቧል፡፡