ክልሉ ለድርቅ አደጋ የሚዉል ተጨማሪ 40 ሚሊዮን ብር በጀት መደበ

ክልሉ ለድርቅ አደጋ የሚዉል ተጨማሪ 40 ሚሊዮን ብር በጀት መደበ
ክልሉ ለድርቅ አደጋ የሚዉል ተጨማሪ 40 ሚሊዮን ብር በጀት መደበ

የካቲት 24/2014 (ዋልታ) የሶማሌ ክልል መንግሥት ለድርቅ አደጋ የሚዉል ተጨማሪ 40 ሚሊዮን ብር በጀት መመደቡን አስታወቀ፡፡

በክልሉ ርዕሰ መሰተዳድር ሙሰጠፌ ሙሁመድ የሚመራ የድርቅ ምላሽ ዐቢይ ኮሚቴ በዛሬው ዕለት ባደረገው  አሰቸኳይ ስብሰባ በተፈጥሮ ድርቅ አደጋ ለተጎዳው ማህበረሰብ ለውሃና ለምግብ የሚውል ተጨማሪ 40 ሚልዬን ብር እንዲመደብ ወስኗል።

ገንዘቡ  የውሃ ማጓጓዣ፣ የዕለት ደራሽ ምግቦች፣ መድሃኒት እና ለእናቶች የሚሆን የተለያዩ የተመጣጠነ ምግቦች መግዣ የሚውል መሆኑን የክልሉ መንግሥት የኮሚኒኬሽን ቢሮመረጃ አመልክቷል።

የሶማሌ ክልል ለድርቁ ምላሽ ለመስጠት እስካሁን ከ1 ነጥብ 5 ቢልዮን ብር በላይ በመመደብ ርብርብ በማድረግ ላይ እንደሚገኝም ተገልጿል፡፡