ሩሲያና አሜሪካ በብጹዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ መርቆሬዎስ ዕረፍት የተሰማቸውን ሃዘን ገለጹ

የካቲት 25/2014 (ዋልታ) ሩሲያ እና አሜሪካ 4ኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብጹዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ መርቆሬዎስ ዕረፍት የተሰማቸውን ሃዘን ገለጹ።

በኢትዮጵያ የሩሲያ ኢምባሲ ባወጣው የሀዘን መግለጫ ብጹዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ መርቆሬዎስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን በመጠበቅና በማጎልበት የተጫወቱት ሚና እጅግ የላቀና ትሩፋቱም ውድ ነው ብሏል።

ብጹዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ መርቆሬዎስ ዕረፍትም ለመላው የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ሀዘን ነው ያለ ሲሆን ከመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር አዝነናል ሲል መልዕክቱን አስተላልፏል።

በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ በበኩሉ ብጹዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ መርቆሬዎስ ዕረፍት የተሰማውን ሀዘን በመግለጽ መጽናናትን ተመኝቷል።