በገንዘብ ሚኒስትሩ የተመራ ልዑክ ጅግጅጋ ገባ

የካቲት 27/2014 (ዋልታ) በገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሺዴ የተመራው የሚኒስትሮች የልዑካን ቡድን ጅግጅጋ ከተማ ገብቷል።
የልዑካን ቡድኑ ጅግጅጋ ከተማ ገራድ ዊል ዋል ኤርፖርት ሲደርስ በሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ ሙሀመድ እና በሌሎች የሥራ ኃላፊዎች አቀባበል ተደርጎለታል።
ልዑካን ቡድኑ የገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሺዴ፣ የብሔራዊ ባንክ ገዢ ይናገር ደሴ (ዶ/ር)፣ የመስኖና ቆላማ አካባቢዎች ሚኒስትር አይሻ መሀመድ፣ የፕላን እና ልማት ሚኒስትር ፍፁም አሰፋ (ዶ/ር) እንዲሁም የዓለም ባንክ የኢትዮጵያ፣ ሱዳን፣ ኤርትራ እና ደቡብ ሱዳን ዋና ዳይሬክተር ኡስማን ዲዮን እና ከአፍሪካ ልማት ባንክ አብዱል ካማራን ያካተተ መሆኑን የሶማሌ መገናኛ ብዙኃን ዘግቧል።
የልዑካን ቡድኑ በክልሉ በተከሰተው ድርቅ ዙሪያ ከክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ ሙሀመድ እና ከሌሎች የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ጋር ውይይት እንደሚያደርግ ተጠቀሟል።