የኩታ ገጠም ግብርና ከተጀመረ ወዲህ አርሶ አደሮች የላቀ ምርት እየሰበሰቡ ነው – ጠ/ሚ ዐቢይ

የካቲት 27/2014 (ዋልታ) በኢትዮጵያ ኩታ ገጠም ግብርናን በማጠናከር የበጋ መስኖ ስንዴን ማምረት ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ አርሶ አደሮች የላቀ ምርት መሰብሰብ መቻላቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አስታወቁ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ ባሰፈሩት መልዕክት የኩታ ገጠም ግብርና ወደፊትም አስፈላጊው ድጋፍ እየተደረገለት ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።