በ5.6 ቢሊየን ብር የተገነባው አዳማ ቆርቆሮ ፋብሪካ የማስፋፊያ ፕሮጀክት ተመረቀ

አዳማ ቆርቆሮ ፋብሪካ የማስፋፊያ ፕሮጀክት

የካቲት 28/2014 (ዋልታ) የአዳማ ቢዝነስ ግሩፕ በ5 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር ያስገነባውን አዳማ ቆርቆሮ ፋብሪካ የማስፋፊያ ፕሮጀክት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት ተመረቀ።

ማስፋፊያው በ2008 ዓ.ም የተጀመረ ሲሆን ለ3 ሺሕ ሰዎች የሥራ እድል መፍጠር የሚችልና በሙሉ አቅሙ ሲያመርት ከ1.2 ሚሊዮን ቶን በላይ ማምረት የሚችል የብረታ ብረት ፈብሪካ መሆኑ ተጠቁሟል።

ፋብሪካው ከዚህ ቀደም በ2006 ዓ.ም በ2 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር የማስፋፊያ ግንባታ አከናውኗል።

ፋብሪካው በብረታ ብረት ኢንዱስትሪ ዘርፍ መሠረታዊ ለውጥ ማምጣትና የኢንዱስትሪ ልህቀት ማዕከል የመሆን ትልም ይዞ እየሠራ እንደሚገኝ ከተቋሙ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

በምረቃ ስነ ሥርዓቱ ላይ የፌዴራልና የክልል የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ ባለሃብቶችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

አስታርቃቸው ወልዴ (ከአዳማ)

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW