ዋሽ የውጊያ ቴክኒክ ትምህርት ቤት በተለያዩ ሙያዎች ያሠለጠናቸውን ባለሙያዎች እያስመረቀ ነው

መጋቢት 2/2014 (ዋልታ) አዋሽ የውጊያ ቴክኒክ ትምህርት ቤት በተለያዩ የሜካናይዝድ ሙያዎች፣ በከባድ እና ቀላል መኪና አሽከርካሪነት ያሠለጠናቸውን ባለሙያዎች በዛሬው ዕለት እያስመረቀ ነው።

በምረቃ ስነ ሥርዓቱ ላይ የምድር ኃይል ጠቅላይ መምሪያ ምክትል አዛዥ ለሰው ሀብት ሜጀር ጄኔራል እንዳልካቸው ወልደኪዳን እና የማሰልጠኛ ትምህርት ቤቱ አዛዥ ብርጋዲየር ጄኔራል ተመስገን አቦሴን ጨምሮ ከፍተኛ ወታደራዊ እና የአካባቢው የመስተዳድር አካላት ተገኝተዋል፡፡

አዋሽ የውጊያ ቴክኒክ ትምህርት ቤት በኢትዮጵያ ብቸኛው የወታደራዊ ሜካናይዝድ ማሰልጠኛ ተቋም ሲሆን በምሥራቅ አፍሪካ ተመራጭ እና ግንባር ቀደም የሥልጠና ማዕከል ለመሆን በመሥራት ላይ እንደሚገኝ ከመከላከያ ሠራዊት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።