የብልፅግና ፓርቲ ጉባኤ እና ተያያዥ ጉዳዮች በስኬት እንዲጠናቀቁ ዝግጅት መደረጉን የጋራ ግብረ-ኃይል አስታወቀ

መጋቢት 2/2014 (ዋልታ) የብልፅግና ፓርቲ ጉባኤ እና ተያያዥ ጉዳዮች በስኬት እንዲጠናቀቁ የፀጥታ አካላት አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት አጠናቀው ወደ ሥራ መግባታቸውን የፀጥታ እና ደኅንነት የጋራ ግብረ-ኃይል አስታውቋል።

አዲስ አበባ ከዛሬ መጋቢት 2 ቀን 2014 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ጀምሮ እስከ መጋቢት 4 ቀን 2014 ዓ.ም አንደኛውን የብልፅግና ፓርቲ ጉባኤ እያስተናገደች ትገኛለች።

ጉባኤውን ተከትሎ መጋቢት 2 ቀን እና መጋቢት 5 ቀን 2014 ዓ/ም በአዲስ አበባ ልዩ ልዩ ፕሮግሞች ይካሄዳሉ።

ጉባኤው እና ተያያዥ ጉዳዮች በስኬት እንዲጠናቁ የፀጥታ አካላት አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት አጠናቀው ወደ ሥራ መግባታቸውን የፀጥታ እና ደኅንነት የጋራ ግብረ-ኃይል አስታውቋል።

በዚህ መሠረት መጋቢት 2 ቀን 2014 ዓ.ም ምሽት አራት ኪሎ አካባቢ የሚካሄደው ፕሮግራም ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ከተለያዩ አቅጣጫዎች ወደ አራት ኪሎ የሚወስዱ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ የሚሆኑ መንገዶችን ይፋ ተደርገዋል።

  • ከፍል ውሃ ወደ ሸራተን ሆቴል
  • ከኦርማ ጋራዥ በሸራተን ሆቴል ወደ ንግድ ማተሚያ
  • ከቴዎድሮስ አደባባይ ወደ ኮንሰን
  • ከአምባሳደር መናፈሻ ወደ ሸራተን ሆቴል

በተመሳሳይ መጋቢት 5 ቀን 2014 ዓ/ም የሚካሄደው ተመሳሳይ ፕሮግራም ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ድረስ ወደ አራት ኪሎ የሚወስዱ መንገዶች፡-

  • ከቀበና በቤልኤር ወደ አራት ኪሎ የሚወስደው መንገድ ቤልኤር መብራት
  • ከስድስት ኪሎ ወደ አራት ኪሎ የሚወስደው መንገድ ቅድስተ ማርያም ትራፊክ መብራት
  • ከፒያሳ በሰባ ደረጃ ቅድስተ ማርያም የሚወስደው መንገድ አራዳ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ቢሮ
  • ከቴዎድሮስ አደባባይ በእሪ በከንቱ ወደ አራት ኪሎ የሚወስደው መንገድ እሪ በከንቱ መብራት
  • ከአዋሬ ገበያ በጥይት ቤት አራት ኪሎ የሚወስደው አዋሬ አደባባይ
  • ከኮንሰን ወደ ፓርላማ የሚወስዱት መንገዶች በተጠቀሱት ቀናት ዝግጅቶቹ ተጀምሮ እስከሚጠናቀቁ ድረስ ለተሽከርካሪ ዝግ ስለሚሆኑ አሽከርካሪዎች አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ እና ለትራፊክ ፖሊስ አባላት ትእዛዝ አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርጉ ፀጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይል አስታውቋል።