ኩሪፍቱ ሪዞርት አዋሽ በይፋ ሥራ ጀመረ

መጋቢት 7/2014 (ዋልታ) የአዋሽ ፓርክን ማዕከል ያደረገው ኩሪፍቱ ሪዞርት አዋሽ በይፋ ሥራ መጀመሩ ተገለጸ፡፡

የኦሮሚያ ባህል እና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ሰአዳ ኡስማን ኩሪፍቱ ሪዞርት በአዋሽ ፓርክ መሰራቱ ለአገር ጠቃሚ የሆኑ የተፈጥሮ ሀብቶችን አውቆ ለሌላው ዓለም ከማሳወቅ አንፃር ፋይዳው የጎላ ነው ብለዋል፡፡

አገር ሊያድግ የሚችለው በባለሃብቶች ተሳትፎ በመሆኑ መሰል ተግባራት ሊበረታቱ እንደሚገባም ጠቁመዋል።

ኩሪፍቱ ሪዞርት ላለፉት 20 ዓመታት በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች በዘርፉ ዓለም ዐቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ አገልግሎቶች ሲሰጥ መቆየቱ ተገልጿል፡፡

ሪዞርቱ ለአገር ውስጥ እና ለውጭ እንግዶች ምቹ እንዲሆን ታስቦ መሰራቱን እና 3 ሺሕ ለሚሆኑ ወጣቶች የሥራ እድል መፍጠሩን የሪዞርቱ ባለቤት ታዲዮስ ጌታቸው ገልፀዋል።

በቁምነገር አሕመድ