አትሌት ሰለሞን እና ለሜቻ በሰርቢያ ቤልግሬድ የዓለም የቤት ውስጥ የአትሌቲክስ ሻምፒዮን ለፍጻሜ አለፉ


መጋቢት 9/2014 (ዋልታ)
በሰርቢያ ቤልግሬድ የዓለም የቤት ውስጥ የአትሌቲክስ ሻምፒዮን በወንዶች 3 ሺሕ ሜትር አትሌት ሰለሞን ባረጋ እና ለሜቻ ግርማ ለፍጻሜ አለፉ፡፡
ከደቂቃዎች በፊት በተጠናቀቀው የ3 ሺሕ ሜትር የወንዶች የማጣሪያ ውድድር አትሌት ሰለሞን እና ለሜቻ ግርማ ከየምድባቸው አንደኛ በመውጣት ወደ ፍጻሜ ማለፋቸውን አረጋግጠዋል፡፡
በዚህ መሰረት አትሌት ሰለሞን ባረጋ እና ለሜቻ ግርማ እሁድ በሚደረገው የፍፃሜ ውድድር ላይ ኢትዮጵያን ወክለው ይሳተፋሉ፡፡
በማጣሪያው በምድብ 3 ተሳትፎ የነበረው ውድድሩን በአሸናፊነት ለማጠናቀቅ ከፍተኛ ግምት ተሰጥቶት የነበረው አትሌት በሪሁ አረጋ 6ኛ መውጣቱን ተከትሎ ከውድድሩ ተሰናብቷል፡፡
በሻምፒዮናው ዛሬ ምሽት 4፡25 ኢትጵያዊያን አትሌቶች የሚጠበቁበት የ3 ሺሕ ሜትር የሴቶች የፍጻሜ ውድድር ይካሄዳል፡፡
በውድድሩ አትሌት ለምለም ኃይሉ፣ አትሌት ዳዊት ስዩም እና አትሌት እጅጋየሁ ታዬ ይሳተፋሉ፡፡
በመሰረት ተስፋዬ
ለፈጣን መረጃዎች፦
ቴሌግራም https://t.me/WALTATVEth
አብራችሁን ስላላ