አዲስ ተሿሚ አምባሳደሮች የ100 ቀናት የሥራ እቅድ አቀረቡ

መጋቢት 10/2014 (ዋልታ) በቅርቡ ሹመት የተሰጣቸው አምባሳደሮች በመጀመራዎቹ 3 ወራት የሚያከናውኗቸውን የሥራ እቅድ አቅርበዋል።

አምባሳደሮቹ የ100 ቀናት እቅዶቻቸውን ያቀረቡት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን በተገኙበት ሲሆን በቀረቡት እቅዶች ላይ ውይይት ተደርጎ አስተያየት እንዲሰጥባቸው ተደርጓል።

ሚኒስትሩ አምባሳደሮቹ የተመደቡባቸውን አገራት ማኅደር እና አሰላለፋቸውን በሚገባ በመረዳት የኢትዮጵያን ፍላጎት ያገናዘበ ውጤታማ ሥራ እንዲያከናውኑ ማሳሰባቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽሕፈት ቤት መረጃ አመላክቷል፡፡