የአፋር ክልል ምክር ቤት 6ኛ የሥራ ዘመን አንደኛ መደበኛ ጉባኤ ተጀመረ

የአፋር ክልል ምክር ቤት

መጋቢት 12/014 (ዋልታ) የአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ምክር ቤት ስድስተኛ የሥራ ዘመን አንደኛ ዓመት አንደኛ መደበኛ ጉባኤ ዛሬ በሠመራ ከተማ ተጀመረ።

ጉባኤው እስከ መጋቢት 14 ቀን 2014 ዓ.ም በሚያደርገው ቆይታ በተለያዩ ወቅታዊ አጀንዳዎች ዙሪያ እንደሚመክር ይጠበቃል።

የአስፈጻሚ አካላት የስድስት ወራት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ላይ በመወያየት ቀጣይ አቅጣጫዎችንም ማስቀመጥ ከምክር ቤቱ ጉባኤ አጃንዳዎች መካከል እንደሚገኙበት ኢዜአ ዘግቧል።