ጨፌ ኦሮሚያ ቡሳ ጎኖፋ የተሰኘ አዲስ አዋጅ አፀደቀ

ቡሳ ጎኖፋ

መጋቢት 13/2014 (ዋልታ) ጨፌ ኦሮሚያ እያካሄደ ባለው 1ኛ ዓመት 6ኛ የሥራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ጉባኤ ቡሳ ጎኖፋ የተሰኘ አዲስ አዋጅ አፀደቀ።

አዋጁ ቀደም ሲል በገዳ ሥርዓት ውስጥ ያለና የቆየ ሥርዓት ሲሆን የሕዝቦች የመረዳዳት እና መደጋገፍ ባህል የሚያሳድግ እንዲሁም የመስጠት ባህልን የሚያጎለብት ነው ተብሏል።

ስለአዋጁ ያስረዱት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ የኦሮሞን ሕዝብ አቃፊነቱንና የመረዳዳት ባህሉን አንስተዋል።

በተለይም በአሁኑ ወቅት በሀገሪቷ በተስተዋለው ድርቅ እና ጦርነት ወቅት ያሳየውን መደጋገፍ በምሳሌነት አመላክተዋል።

ገዳ የሰው ልጅ መተዳደሪያ እንጂ የፖለቲካ ፓርቲ አይደለም ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ ይህን የመረዳዳት እና የመስጠት ባህልን ለማጠናከር አዋጁ እንዳስፈለገ ገልጸዋል።

በዚህም የኦሮሚያ ክልል ቡሳ ጎኖፋ ሥርዓት አዋጁ በ441 ድምፅ ፀድቋል።

በሚልኪያስ አዱኛ

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW
ቴሌግራም https://t.me/WALTATVEth
ዩቲዩብ https://www.youtube.com/c/WaltaTV/featured
ቲዊተር https://twitter.com/walta_info
አብራችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን!