በሶማሌ ክልል የሚስተዋለውን ሙስና መቅረፍ እንደሚገባ ነዋሪዎች ጠየቁ

መጋቢት 14/2014 (ዋልታ) በጅግጅጋ ከተማ እየተካሄደ በሚገኘው ሕዝባዊ ውይይት በሶማሌ ክልል የሚስተዋለውን ሙስና መቅረፍ እንደሚገባ ነዋሪዎች ጠይቀዋል፡፡

የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ ሙሀመድ፣ የብልፅግና ፓርቲ ሥራ አስፈፃሚ አባል እዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) እና ሌሎች ከፍተኛ የመንግሥት ሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት  በጅግጅጋ ከተማ ሕዝባዊ የውይይት መድረክ እየተካሄደ ሲሆን በክልሉ የሚገኙ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ሕዝቡ በሚፈልጋቸው ጊዜ መገኘት አለመቻላቸው ተነስቷል፡፡

ከነዳጅ ጋር በተያያዘም በህገወጥ መንገድ ወደ ጎረቤት አገር በማሸሽ የሚሰራውን የኢኮኖሚ አሻጥር ለመቅረፍ በትኩረት ሊሰራ እንደሚገባና በዚህ ረገድም ኅብረተሰቡ ተባባሪ ሊሆን እንደሚገባ ተጠቁሟል፡፡

ሱራፌል መንግሥቴ (ከጅግጅጋ)