በሀረሪ ክልል ሕዝባዊ የውይይት መድረክ እየተካሄደ ነው

መጋቢት 14/2014 (ዋልታ) በሀረሪ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ከሀረሪ ክልል ነዋሪዎች ጋር ሕዝባዊ ውይይት እያካሄደ ይገኛል።
ሕዝባዊ ውይይቱ የሀረሪ ክልል ርዕሠ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ እንዲሁም የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈፃሚ አባላት በተገኙበት እየተካሄደ ነው።
የክልሉ መንግሥት ኮሙዩኒኬሽን መረጃ እንደሚያመላክተው በመድረኩ ከኅብረተሰቡ የሚነሱ ጥያቄዎች በአመራሩ ምላሽ ይሰጥባቸዋል ተብሎ እንደሚጠበቅ የክልሉ መንግሥት ኮሙዩኒኬሽን መረጃ አመላክቷል።