በእንጅባራ ከተማ የሕዝብ ውይይት እየተካሄደ ነው

መጋቢት 14/2014 (ዋልታ) “የፈተናዎች መብዛት ከብልጽግና ጉዟችን አያስቆመንም” በሚል መሪ ቃል በአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር እንጅባራ ከተማ የሕዝብ ውይይት እየተካሄደ ነው።
በውይይት መድረኩ የክልል፣ የዞንና የወረዳ አመራሮች፣ ከእንጅባራ ከተማና ከባንጃ ወረዳ አጎራባች ቀበሌ የተውጣጡ የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች እየተሳተፉበት ነው።
ውይይቱን በንግግር የከፈቱት የአማራ ከልል ርዕሰ መስተዳድር ጽሕፈት ቤት ኃላፊ እርዚቅ ኢሳ የውይይት መድረኩ በብልጽግና ፓርቲ 1ኛ ጉበኤ አሉ የተባሉ ችግሮች ኅብረተሰቡ ከሚያነሳቸው ችግሮች ጋር ይጣጣማሉ፤ የቀሩ ችግሮችስ አሉ ወይ? በማለት ለማካተትና መንግሥትና ሕዝብ መክሮ እንዲፈታ ማድረግን ያለመ ነው ብለዋል፡፡
በተጨማሪም ሰላምና ደኅንነት፣ የኑሮ ውድነት፣ ሌብነትና ስርቆት፣ አገልግሎት አሰጣጥ፣ ሥራ አጥነትና በአጠቃላይ በገጠሙን ፈተናዎች እንዲሁም የብልጽግና ጉዟችንን በማያስቀሩ ጉዳዮች ላይ እንመክራለን ማለታቸውን የብልጽግና ፓርቲ የአዊ ዞን ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት መረጃ አመላክቷል፡፡