በሰመራ ከተማ ሕዝባዊ ውይይት እየተካሄደ ነው

በሰመራ ሕዝባዊ ውይይት

መጋቢት 15/2014 (ዋልታ) በአፋር ክልል በብልጽግና ፓርቲ ቀጣይ አቅጣጫዎች እና በ1ኛ ጉባኤ ውሳኔዎች ዙሪያ በሰመራ ከተማ ሕዝባዊ የውይይት መድረክ እየተካሄደ ነው።

በውይይት መድረኩ በፓርቲው 1ኛ መደበኛ ጉባኤ በተቀመጡ አቅጣጫዎች፣ ውሳኔዎችና አቋሞች ዙሪያ የጋራ ግንዛቤ እንደሚፈጠር ይጠበቃል።

በውይይቱም የክልሉ ርዕሰ መስተዳድርና የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል አወል አርባ፣ የገንዘብ ሚኒስትር እና የብልፅግና ፓርቲ ሥራ አስፈፃሚ አሕመድ ሽዴ እና የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ተስፋዬ ይገዙ አና ሌሎች የክልሉ ሥራ ኃላፊዎችና የክልሉ የኅብረተሰብ ክፍሎች መገኘታቸውን ከክልሉ መገናኛ ብዙኃን ኤጄንሲ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW