ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ለተሿሚ አሞባሳደሮች የሥራ መመሪያ ሰጡ

ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ

መጋቢት 15/2014 (ዋልታ) ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ለተሿሚ አሞባሳደሮች የሥራ መመሪያ ሰጥተዋል።

ወደተለያዩ አገራት የሚሄዱ አምባሳደሮች የአሸናኘትና የቃለ መሃላ መርሃ ግብር እየተካሄደ ሲሆን በዝግጅቱ ላይ የተገኙት ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ዲፕሎማሲ የአንድ አገር ቀጣይነትን የሚያረጋግጥ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ፕሬዝዳንቷ ለአማባሳደሮች በሰጡት የሥራ መመሪያ የኛን ጥቅም በማስከበር ከሎሎች አገራት ጋር መልካም ግንኙነት መፍጠር እንደሚገባ ገልጸው ኢትዮጵያን መወከል ምንኛ ትልቅ ክብር እንደሆነ ልትረድት ይገባል ሲሉም አክለዋል።

የአገር ገፅታ ማጉላትና አሁን ያለውን የዲፕሎማሲ ግንኙነት ለማዳበር እለት ተእለት መስራት ያስፈልጋልም ነው ያለት።

የአገር ክብርና ፍቅር የሕዝብ አደራ ሁሌም በልባችሁ እንድታሳድሩ አደራ እላለሁ ሲሉም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

በሳራ ስዩም