ብልፅግና ፓርቲ ከምእራብ ሸዋ ዞን ከተውጣጡ የማኅበረሰብ ክፍሎች ጋር እየተወያየ ነው

መጋቢት 16/2014 (ዋልታ) ብልፅግና ፓርቲ ከምእራብ ሸዋ ዞን ከተውጣጡ የማኅበረሰብ ክፍሎች ጋር በአምቦ ከተማ ሕዝባዊ ውይይት እያካሄደ ይገኛል፡፡
በውይይቱም የትራንስፖርት ሚኒስትር ዴኤታ ካሳሁን ጎፌ፣ የአምቦ ከተማ ከንቲባ ሃጫሉ ገመቹ፣ አባገዳዎች፣ ሀደ ሲንቄዎች እንዲሁም ሌሎች የማኅበረሰብ ክፍሎች ተሳትፈዋል፡፡
ፓርቲው በአንደኛው ጠቅላላ ጉባኤ ወቅት በተወያየባቸው አንኳር ጉዳዮች ላይ ለነዋሪዎች ማብራሪያ ተሰጥቷል::
በመድረኩ ከማኅበረሰቡ የሚነሱ ጥያቄዎች ምላሽ እንደሚሰጥባቸው የተገለፀ ሲሆን ፓርቲው ባሳለፋቸው ውሳኔዎች እና ባስቀመጣቸው አቅጣጫዎች ላይ መግባባትን ለመፍጠር በሚያስችሉ ነጥቦች ዙሪያም ምክክር ይደረጋል ተብሏል::
ሔብሮን ዋልታው (ከአምቦ)