የአማራ ክልል ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤ 2ኛ ቀኑን ቀጥሏል

መጋቢት 16/2014 (ዋልታ) የአማራ ክልል 6ኛ ዙር 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ጉባኤ 2ኛ ቀኑን ቀጥሏል፡፡
የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ/ር) ባቀረቡት የ6 ወራት የሥራ አፈፃፀም ላይ የምክር ቤት አባላት ጥያቄ እያቀረቡ ይገኛሉ።
ሥራ አጥነት፣ የመጠጥ ውሃ ግንባታና አቅርቦት አፈፃፀም፣ የመልካም አስተዳደር እና የአገልግሎት አሰጣጥ፣ ሙስና እንዲሁም የማዳበሪያ አቅርቦት ችግር ከአባላቱ ከተነሱ ጥያቄዎች መካከል ይጠቀሳሉ፡፡
ምንይሉ ደስይበለው (ከባሕር ዳር)