የኦፌኮ 2ኛ መደበኛ ጉባኤ የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች በተገኙበት እየተካሄደ ነው

የኦፌኮ 2ኛ መደበኛ ጉባኤ

መጋቢት 17/2014 (ዋልታ) የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግረስ ኦፌኮ 2ኛ መደበኛ ጉባኤ የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች በተገኙበት እየተካሄደ ነው፡፡

በጉባኤው ከተገኙ የፖሊቲካ ፓርቲ ተወካዮች መካከል የኦሮሞ ነጻነት ግምባር (ኦነግ) ተወካይ ጀቤሳ ገቢሳ በኦነግ እና ኦፌኮ የኦሮሞ ሕዝብ ስኬት የጋራ መሆኑን እንደሚያምን ገልጸዋል።

ለትግሉ ሁለቱ ፓርቲዎች የጋራ መስዋዕትነት ከፍለዋል ያሉት የፓርቲው ተወካይ  ስኬታችንም የወል ብለዋል።

በጉባኤው መልዕክታቸውን ካስተላለፉት የተለያዩ ፖለቲካ ፓርቲዎች ተወካዮች መካከል ኅብር ኢትዮጵያ፣ የአፋር ሕዝብ ነጻነት ፓርቲ፣ የአገው ብሔረሰብ ፓርቲና የኦሮሞ ነጻነት ግምባር (ኦነግ) ይገኙበታል።

ለሁለት ቀናት የሚካሄደው የኦፌኮ ጉባኤ የፓርቲው ሊቀመንበር መራራ ጉድና (ፕ/ር)፣ ምክትል ሊቀመንበር በቀለ ገርባ እንዲሁም ጀዋር ሙሀመድን ጨምሮ ሌሎች የፓርቲው አባላትና ከተለያዩ ፓርቲዎች የተወከሉ አካላት በተገኙበት እየተካሄደ ይገኛል።

በዱጋሳ ፉፋና ታምራት ደለሊ

 

ለፈጣን መረጃዎች፦

ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW

ቴሌግራም https://t.me/WALTATVEth

ዩቲዩብ https://www.youtube.com/c/WaltaTV/featured

ቲዊተር https://twitter.com/walta_info

አብራችሁን ስለሆናችሁ እናመሰግናለን!