የድሬዳዋ ሳምንታዊ የብስክሌተኞችና እግረኞች ቀን ማስጀመሪያ መርኃ-ግብር እየተካሄደ ነው

መጋቢት 18/2014 (ዋልታ) የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ሳምንታዊ የብስክሌተኞችና እግረኞች ቀን ማስጀመሪያ መርኃ-ግብር በለገሀር አደባባይ እየተካሄደ ነው።
በመርኃ-ግብሩ ላይ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዳግማዊት ሞገስ፣ የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሀርን ጨምሮ ከፍተኛ አመራሮችና ነዋሪዎች እየተሳተፉ መሆኑን የከተማ አስተዳደሩ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን መረጃ አመላክቷል።