ከንቲባ አዳነች አቤቤ በልደታ ክፍለ ከተማ የተሰሩ 82 የተለያዩ የልማት ፕሮጀክቶችን መረቁ

መጋቢት 18/2014 (ዋልታ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በልደታ ክፍለ ከተማ የጤና፣ ትምህርት፣ ስፖርት ማዘውተሪያን ጨምሮ ግንባታቸው የተጠናቀቁ 82 የተለያዩ ፕሮጀክቶችን መረቁ።
በክፍለ ከተማው የተመረቁት 82 ፕሮጀክቶች የኅብረተሰቡን የልማትና የመልካም አስተዳደር ችግሮች በዘላቂነት ለመፍታትና ተጠቃሚ ለማድረግ የተሰሩ መሆናቸው ተገልጿል።
ግንባታቸው ተጠናቆ ከተመረቁት ፕሮጀክቶች መካከል የጤና ተቋማት፣ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች፣ ትምህርት ቤቶች፣ የተማሪ ምገባ አዳራሾች፣ የጋራ መፀዳጃ ቤቶች፣ የወጣት ስብዕና መገንቢያ ማዕከላትና ሌሎችም ይገኙበታል።
ለፕሮጀክቶቹ ግንባታ አጠቃላይ 162 ሚሊዮን ብር ወጪ መደረጉ ታውቋል ሲል የዘገበው ኢዜአ ነው።
በምርቃት መርኃ-ግብሩ ላይ ከንቲባዋን ጨምሮ ሌሎች የአስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም የክፍለ ከተማው ዋና ሥራ አስፈፃሚ ተገኝተዋል።