በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር በድሬዳዋ የአትክልትና ፍራፍሬ ልማትን ጎበኙ

መጋቢት 20/2014 (ዋልታ) በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር በመንግሥታቸው ድጋፍ ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በድሬዳዋ እያካሄደ ያለውን በምርምር የተደገፈ የአትክልትና ፍራፍሬ ልማት ጎብኝተዋል።
በጉብኝቱ የመስኖና የቆላማ አካባቢዎች ሚኒስትር አይሻ መሐመድ ተገኝተዋል።
የእስራኤል አምባሳደር አለልኝ አድማሱና ሚኒስትሯ በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሃርና በሌሎች ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
“በዘርፉ እየተካሄዱ ያሉ የምምር ሥራዎች ምርታማነትን ከማሳደግ ባለፈ ለውጭ ገበያ የሚውሉ ምርቶችን በማምረት የምንዛሬ ገቢን ለማሳደግ ያግዛሉ” ተብሏል።
በቤተሰብ ደረጃ የምግብ ዋስትና በማረጋገጥ ረገድም አስተዋጽኦዋቸው የላቀ መሆኑ ተመላክቷል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።