የኦሮሚያና ሀረሪ ክልል አርሶ አደሮች ተጠቃሚነትን ሊያጠናክሩ በሚችሉ ፕሮጀክቶች ዙሪያ ውይይት ተካሄደ

መጋቢት 21/2014 (ዋልታ) የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ በመስኖና ቆላማ አካባቢዎች ሚኒስትር አይሻ መሐመድ ከተመራው ልዑክ ጋር የአርሶ አደሩን ተጠቃሚነት ማጎልበት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል።

በውይይታቸውም በተለይ የኦሮሚያና የሀረሪ ክልል አርሶ አደሮች ተጠቃሚነትን ሊያጠናክሩ የሚችሉ ፕሮጀክቶችን እውን ማድረግ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ትኩረት አድርገዋል።

እውን ለማድረግ የታሰቡት ፕሮጀክቶችም ግድብ እና የንፁህ መጠጥ ውሃ መሆናቸው የተገለፀ ሲሆን ፕሮጀክቶቹም በሁለቱ ክልል አዋሳኝ በሆነው ኤረር ወረዳ አካባቢ እንደሚከናወን ተጠቁሟል።

ከዚህ በተጨማሪም የአርሶ አደሩን ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል።

በተለይም በእስራኤል መንግሥት የሚደገፈው ፌር ፕላኔት የተሰኘው ፕሮግራም አማካኝነት ለአርሶ አደሩ የተሻሻሉ ዝርያዎች እንደሚቀርቡ ተመላክቷል።

በውይይቱ የፌዴራልና ክልል ከፍተኛ አመራሮችን ጨምሮ በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር አለልኝ አድማሱ እና የሀረማያ ዩኒቨርሲቲ የሥራ ኃላፊዎች መሳተፋቸውን ከክልሉ መንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW