ሚኒስቴሩ ለቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የ100 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ

መጋቢት 21/2014 (ዋልታ) የከተማ እና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በጸጥታ ችግር ምክንያት ለተፈናቀሉ ዜጎች የሚውል የ100 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደርጓል።

የከተማ እና መሠረተ ልማት ሚኒስትሯ ጫልቱ ሳኒ ድጋፉን ለቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር አሻድሊ ሀሰን አስረክበዋል።

ርዕሰ መሥተዳድር አሻድሊ ሚኒስቴሩ ላደረገው ድጋፍ በክልሉ መንግሥትና ሕዝብ ስም ምስጋና አቅርበዋል።

የክልሉ መንግሥት ካማሺና መተከል ዞኖችን ጨምሮ በክልሉ የተፈናቀሉ ዜጎችን ለማቋቋም አቅዶ አየሠራ ባለበት በዚህ ወቅት የተደረገለት ድጋፍ ትልቅ አቅም ይሆናል ብለዋል።

ሚኒስትሯ በበኩላቸው ከቀያቸው የተፈናቀሉ ዜጎችን ተመልሰው መቋቋም ያለባቸው በእኛው በራሳችን በመሆኑ ሁሉም የበኩሉን እንዲወጣ መጠየቃቸውን የክልሉን መንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጠቅሶ ኢፕድ ዘግቧል፡፡