ፓርኩ በጦርነቱ ሳቢያ ከግማሽ ቢሊየን ብር በላይ የሚገመት ጉዳት ደርሶበታል

መጋቢት 21/2014 (ዋልታ) የኮምቦልቻ ኢንዱስትሪ ፓርክ በጦርነቱ ሳቢያ ከግማሽ ቢሊየን ብር በላይ የሚገመት ጉዳት እንደደረሰበት ተገለጸ።

የጋዜጠኞች ቡድን በፓርኩ ጉብኝት እያደረገ ሲሆን 4 ማከማቻዎች ሙሉ በሙሉ መውደማቸው፣ መሰረታዊና ለወጪ ንግድ የሚሆኑ እቃዎች መዘረፋቸውን ተመልክተዋል፡፡

የኢንዱስትሪ ፓርኩ ሥራ አስኪያጅ አሕመድ ሰኢድ ፓርኩ ካጋጠመው ችግር በኋላ ወደ ሥራ መመለሱን ገልጸው በበጀት ዓመቱ 3 ነጥብ 4 ሚሊየን ዶላር የሚያወጡ እቃዎች ወደ ውጪ መላኩንና ገቢ ማስገኘት መቻሉ ጠቁመዋል።

የኮምቦልቻ ኢንዱስትሪ ፓርክ በ93 ሚሊየን ዶላር ፈሰስ ተደርጎ የተገነባ ሲሆን በውስጡ 4 ካምፓኒዎች ሲኖሩት 3 ሺሕ 200 ለሚሆኑ ዜጎች የሥራ እድል የፈጠረ ነው ተብሏል፡፡

ይሁን እንጂ ከጦርነቱ በኋላ 2 ሺሕ 100 ሰራተኞች ብቻ ወደ ሥራቸው እንዲመለሱ መደረጉ ተገልጿል።

ዙፋን አምባቸው (ከኮምቦልቻ)